Advent 2021

Advent 2021

Thursday, 06 January 2022 08:28

ቀን 14:- አማኑኤል

Written by

በምንም ነገር ውስጥ እያለፍሽ ቢሆን እግዚአብሔር አስቀድሞ ለአንቺ ያዘጋጀውን መልካም ሥራ ለመሥራት በክርስቶስ የተፈጠርሽ የእግዚአብሔር እጅ ሥራ እንደሆንሽ አስታውሺ።

Wednesday, 05 January 2022 08:21

ቀን 13:- ቀላል ግርማዊነት

Written by

መንፈስ ቅዱስ ለነፍሳችን ሕይወት እየሰጠ በጸጋ ወዳለው መዳን ይመራናል፤ ይህ ቸር መንፈስ በኢየሱስ የተሰጠንን ይህንን ተስፋ ያረጋግጥልናል፣ በድካማችን እየደገፈ ከባድና ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታዎችን እንድናልፍ ያደርገናል። 

Tuesday, 04 January 2022 09:44

ቀን 12:- የማርያም ምሳሌ

Written by

ከእግዚአብሔር ቃል ስንቀበል በእግዚአብሔር በመመረጣችን የሚሰማውን ክብር ብዙዎቻችን ልናውቀው እንችላለን። “አሜን” እያልን በደስታና በሐሴት እንቀበለዋለን። ነገር ግን የተስፋ ቃሉ እስኪፈጸም ጉዞው ባልጠበቅነው ተራራዎችና ሸለቆዎች መካከል ይወስደናል። በዚህ ሁሉ እንዴት ልንጸና እንችላለን?

Monday, 03 January 2022 10:04

ቀን 11:- የፍቅር አምላክ

Written by

የኢየሱስን ወደ ምድር መምጣት በማስብበት ጊዜ የፍቅሩን ልክ ያሳየኛል። ሊደረስበት በማይቻል ከፍታ ያለው አምላክ ፍጥረቱን ሊታደግ የወረደበት ምክንያት ፍቅር ነው! ዛሬ ባለሽበት ሁኔታ ውስጥ ይህን ጥልቅ ፍቅር እንድታስቢ አበረታታሻለሁ። 

Friday, 31 December 2021 00:00

ቀን 10:- እንደተራ ሰው

Written by

“ይጸልልልሻል” የሚለውን ቃል ትርጉም ስንመለከት “መጠበቅ፣ መጋረድ፣ በጠባቂ ተጽዕኖ ሥር ማድረግ” የሚል ሃሳብ ነው። ይህ ማለት ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ጥበቃ ሥር፣ በእርሱ ተጋርዳና ተከልላ እንደምትኖር ማረጋገጫ ተሰጥቷታል። 

Thursday, 30 December 2021 00:00

ቀን 9:- ልናከብር የሚገባው

Written by

በየዓመቱ ገናን ስናከብር እንደማንኛውም ሌላ በዓልና የእረፍት ጊዜ ብቻ አናስበው፤ እንደመደበኛ ልደትም አንቁጠረው። ወንድሞችና እህቶች፣ የምናከብረው አምላክ ሰው ሆኖ በእኛ መካከል ማደሩን ነው! የምናከብረው ለዘመናት የተሰጠውን ተስፋ ፍጻሜ ነው። 

Wednesday, 29 December 2021 00:00

ቀን 8:- ቃል ሥጋ ሆነ

Written by

እንደ አዲስ እናት የ6 ወር ልጄ ነገሮችን ለመያዝ፣ ለመገለባበጥ ሲሞክር፤ እንቅልፉ ሲመጣ ሲነጫነጭ... እያየሁ ኢየሱስ ልክ እንደዚህ ሕጻን ሆኖ በመካከላችን ማደሩን እያሰብኩ እደነቃለሁ። በመጀመሪያ የነበረውና በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረው ቃል እንደአንድ አቅም የሌለው ሕጻን ሆኖ ወደኛ መጣ - እንዴት አስደናቂ ነው!

የአዳኙን የክርስቶስን ልደት በምናከብርበት በዚህ በተወደደ ጊዜ ጌታና ቤተሰቦቹ የከፈሉትን ዋጋ ማስታወስ ግራ በተጋባንበት ነገር ላይ የእግዚአብሔር መገኘት እንዳለ በመተማመን ወደርሱ እንድንቀርብ ያበረታታናል፤ ጠላት ሕጻኑን ኢየሱስን ሊያጠፋው አጥብቆ ቢጥርም የእግዚአብሔር ጥበቃ በርሱ ላይ ስለነበረ አመለጠ፡፡  

Monday, 27 December 2021 00:00

ቀን 6:- እግዚአብሔር አስቆመኝ

Written by

እግዚአብሔር ግን ለተለያየ አላማ ከተለያየ አይነት ሩጫችን ያስቆመናል። መልዐኩ ገብርኤል ለማርያም “እነሆ፤ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ” ሲላት፣ ለራሷ ከዮሴፍ ጋር ያሰበችውን ወይም ያቀደችውን ህይወት እንዲሁም ስለ ወደ ፊት ህይወቷ የነበራትን ሐሳብ አስቁሞታል። ግን ማርያም የህይወቷን አስደንጋጭ መቀያየር አይታ ያደረገችው ነገር እኔም፣ እኛም የምንማርበት ነው። ማርያም አምላኳን ጥያቄ ጠየቀች እንጂ አምላኳን ጥያቄ ውስጥ አላስገባችውም። ማርያም አምላኳን አመነች። 

የኢየሱስ ምክር፣ መመሪያ ወይም ማጽናኛ በምንፈልገው የሕይወት ዘርፍ ውስጥ ሁሉ በሙላት መገኘት ይችላል፣ ይገኛልም። የእርሱ ጥበብ ምንም ገደቦች የሉትም። ሁሉን የሚያውቅ እና ኃያል የሆነውን አምላክ እንደ አማካሪ ማግኘታችን ለእኛ እጅግ ልዩ ነው።

white-200.png

Serving Ethiopian women by encouraging and exemplifying vulnerable, thought-provoking conversations around the Gospel of Jesus Christ, the mission of the
Church, and the life of a Christian.

Address
:
Golagul Tower
Addis Ababa, Ethiopia

Emailinfo@selahethiopia.org
selahforethiopia@gmail.com

Follow Us

Subscribe to emails from Selah

We have officially launched our website and all our social media platforms. Please join us, follow, and share. Subscribe to our newsletter bringing you regular updates, resources, and everything in between!

Copyright © 2025 Selah Ministries.
Address: Addis Ababa, Ethiopia 
Emailinfo@selahethiopia.org