የጥናታችን ሁለተኛ ሳምንት ላይ ደርሰናል! መጽሐፍ ቅዱስ የእምነት ጀግኖችን የማየት እና የማጥናት ስጦታ ይሰጠናል። ከነዚያም አንዷ ረዓብ ናት፡፡ ረዓብ ዝሙት አዳሪ ነበረች ግን የእምነት ሴት ተብላ በአርአያነት ስሟ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ብዙ ጊዜ ሲጠቀስ እናያለን፡፡ በኢየሱስ የዘር ሐረግ ውስጥ እንዴት እንደገባች ለማየት ሕይወቷን አብረን እናጥና፣ ንቁ እና ሥር ነቀል እምነት ምን እንደሚመስሉም ለማወቅ እንሞክር፡፡ በዚህ ጥናት ውስጥ ጠለቅ ብለው እንዲሄዱ የሚያግዝዎ የጥናት መመሪያ አዘጋጅተናል፡፡
The Bible gives us the wonderful gift of looking on to heroes of faith from the Bible to encourage us; and one of those heroes is Rahab. Rahab was a prostitute and yet her name is mentioned several times in the New Testament as an exemplary woman of faith. Let's study her life together to see how she ended in Jesus' lineage and learn about what active faith— radical faith— looks like. We have prepared a study guide to help you go deeper in this study.