Thursday, 30 December 2021 00:00

ቀን 9:- ልናከብር የሚገባው

Written by

“What we celebrate at Christmas is not so much the birth of a baby (as important as that is). But what’s so significant about the birth of that particular baby is that in this birth we have the incarnation of God himself.” — R.C. Sproul 

ይህንን መልዕክት ሳነበው ተገረምኩ - በገና የምናከብረውን እንዴት አድርጎ አስቀምጦታል! ገናን ስናከብር ሁለት ዓይነት ነገሮች እየሆኑ ይመስለኛል፦ አንደኛው ምዕራባዊ የሆነውን የገና አከባበር አንዳንዶቻችን በመከተል በዓሉን ስለቤተሰብ፣ ስጦታና መሰባሰብ እናደርገዋለን፤ ሌሎቻችን ደግሞ በባህላዊው አስተሳሰብ ተይዘን በታላቁ ክስተት ሳንደነቅ ያልፈናል። በእርግጥ ለዘመናት ክርስትና እንዳስተናገደች አገር “እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ” እንባባላለን፤ ነገር ግን አንዳንዴ ትኩረታችን በሰላምና በጤና መድረሳችን ላይ ብቻ ይሆናል። 

እውነታው ግን - አምላክ ራሶ ሰው መሆኑ፣ አማኑኤል እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚለው የሚያስደንቅ ነገር ነው። በዘፍጥረት 3፡15 ለእባቡ የተነገረው ማስጠንቀቂያ፤ ለኖህ፣ ለአብርሃም፣ ለዳዊት የተሰጠው ተስፋ፤ በመዝሙረ ዳዊት፣ በኢሳይያስ፣ በሚክያስ የተነገሩት ትንቢቶች ሁሉ የሚጠቁሙት ወደዚህ ታላቅ ጊዜ ነው። 

“ነገር ግን የተወሰነው ዘመን በደረሰ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን፣ ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤ ይህም የሆነው የልጅነትን መብት እናገኝ ዘንድ ከሕግ በታች ያሉትን ለመዋጀት ነው።” (ገላትያ 4፡ 4-5) 

በየዓመቱ ገናን ስናከብር እንደማንኛውም ሌላ በዓልና የእረፍት ጊዜ ብቻ አናስበው፤ እንደመደበኛ ልደትም አንቁጠረው። ወንድሞችና እህቶች፣ የምናከብረው አምላክ ሰው ሆኖ በእኛ መካከል ማደሩን ነው! የምናከብረው ለዘመናት የተሰጠውን ተስፋ ፍጻሜ ነው። 

ይህ የሆነው ጌታ በነብዩ የተናገረው እንዲፈጸም ነው፦ ““እነሆ ድንግል ትጸንሳለች፣ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል” ትርጉሙም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” ማለት ነው” (ማቴ. 1፡22-23) 

 

ጸሎት

ጌታ ሆይ፣ በዚህ የገና ወቅት የሠራኸውን ሥራ ታላቅነትና ያሳየኸውን ፍቅር ጥልቀት እንድንረዳ አንቃን! አሜን!

white-200.png

Serving Ethiopian women by encouraging and exemplifying vulnerable, thought-provoking conversations around the Gospel of Jesus Christ, the mission of the
Church, and the life of a Christian.

Address
:
Golagul Tower
Addis Ababa, Ethiopia

Emailinfo@selahethiopia.org
selahforethiopia@gmail.com

Follow Us

Subscribe to emails from Selah

We have officially launched our website and all our social media platforms. Please join us, follow, and share. Subscribe to our newsletter bringing you regular updates, resources, and everything in between!

Copyright © 2024 Selah Ministries.
Address: Addis Ababa, Ethiopia 
Emailinfo@selahethiopia.org