Wednesday, 08 April 2020 18:42

የውትድርና ስልጠና በቤትዎ 

Written by

በአንድ ዘመን ነዉ አሉ አዋቂዎች ሲተርቱ፣ በሕዝቦች ሁሉ ላይ ይነግስ የነበረ አንድ ልዩ “ንጉስ” ነበር። በዘመናት መካከል ምድርና ሞላዋን በውስጡም ያሉትን ፍጥረታት በሙሉ ጠቅልሎ የሚገዛ አቻ የለሽ እንደነበር ይነገራል።

ታድያ በአንድ ባልታሰበ ወቅት በሚገዛቸው “ሕዝቦች” ሁሉ ላይ ያለልዩነት በእኩል የሚያጠቃ የጋራ “ጠላት” መጣባቸው። በወቅቱ ሰው ሁሉ የጦርነቱ ልክ በአይኑ ያየው ነገር ብቻ ይመስለው ነበር። ከአስተሳሰባቸውም ውስንነት የተነሳ ከበስተጀርባ ምንኛ የከፋ ከባድ ዘመን እንዳለ አሻግረው ማየት ተስኖአቸው፥ በዛሬያቸው ላይ ቆመው በአስተሳሰብና በንቃተ ህሊና ድክመት ይረቱ ነበር።

እንዲህ ላለው ዘመንም ድል መንሻ ይሆናቸው ዘንድ፣ በንጉሱ ምርጫ  ጥቂቶችን አስቀድሞ “የጦር መሣሪያ” አስታጥቆ እንደነበር ጭምጭምታ ይሰማ ነበር። ነገር ግን ትጥቁን ይይዙ እንጂ አጠቃቀሙን የማያውቁት፣ ጨርሶም በእጃቸው ስለመኖሩ የዘነጉ ይበዙ ነበር። 

ይህም የሆነው ምናልባት ብዙሃኑ በራሳቸው ዕለት ተዕለት ህይወት ተተብትበው ለዘመናት ይሰጥ የነበረውን የትጥቅ አጠቃቀም ስልጠና ለመውሰድ ቅድሚያ ባለመስጠታቸው ነው። በግለሰቦች የነበሩ መሣሪያዎች እንደ ህፃናት እቃእቃ መጫወቻ ከአላማና ክብራቸው የወረዱ ተራ የቤት ቁስ አካል ሆነው ነበር። 

በዚህም ወቅት፣ ሁኔታ ሁኔታን ጠራና፣ በአለም ያለው ሕዝብ ከደጃፉ ሳይወጣ በቤቱ እንዲከተት አዋጅ ታወጀ። የምድሪቱ ንጉስ ግን በዚህ ወቅት ምስጢራዊ አጀንዳ ነበረው። አስቀድሞ ለመረጣቸው፣ ለወሰናቸው፣ ለለያቸው፣ ለመለመላቸው የመንግሥቱ ወታደሮች ይህን ወቅት “የውትድርና ስልጠና በቤትዎ” በሚል መርሃግብር  የስልጠና ዕድልን ሰጣቸው። ንጉሱ ይህን ያድርግ እንጂ፣ የወታደሮቹ አቀባበል የተለያየ ነበር። 

አንዳንዱ ስንቅና ስልጠናውን ትቶ፣ ሊመጣ የሚችለውን ጦርነትና እልቂት ከወሬ አራጋቢዎች ጋር እያራገበ፣ በአሉባልታ ብቻ እንጂ በተሰጠኝ ጠመንጃ አልደገፍም ብሎ የስልጠና ዕድሉን እየተዘናጋበት ግዜው ያልፍበት ነበር።

ጥቂት የማይባለው ደግሞ፣ የጠላት ማንነትምንጭ ይህ ወይንም ያ ነው በማለት በዘመኑ ማንም እርግጥ በማያውቀው መላምትና ፍልስፍና ተዘፍቆ ነበር። የተመረቀላቸውን ውድ ግዜም፣ ይህ ነገር “የፈጣሪ ቁጣ፣ የዲያቢሎስ ውጊያ፣ ከሃያላን መንግሥት የመጣ” በሚሉ ግምቶች ተወስደው፣ ራሳቸው የመፍትሔ አካል መሆናቸውን ዘንግተው ነበር። 

በተቃራኒው የጠላትን አላማና ጉልበት ንቀው በትምክህት በመሞላት፣ “እኛን አይነካንም ይብላኝ ለሌለው” በሚል ባዶ ድፍረት ለስልጠናው ቦታ ሳይሰጡ የቆዩ ብዙሃን ነበሩ።

የባሰም አለ፣ የቁጭ በሉን አዋጅ ከእውነቱ አርቀው እንደ  “ቁጭ ይበሉ ስራ ይፍቱ” በመውሰድ ቀድሞ የነበረውን እንኳን ጥቂት እውቀት እስኪሸረሸር ድረስ ባለማስተዋል ስንፍና ውስጥ የገቡ ነበሩ።

በአንድ ወገን ደግሞ ያሉት፣ ጠላትን ከስሩ የሚመነጥሩበትን ግላዊ ስልጠና ትተው ለታይታ ያህል ላይ ላዩን ያለ በቂ ልምምድና እውቀት ራሳቸውን እንደ ብቁ ቆጥረው በመዘለል የተቀመጡ ነበሩ። 

ልቦና የሰጣቸው ጥቂቶቹ ግን በረቱ። መመረጣቸውን አስተዋሉ። ቀኖቹን ለዩ። ይህ የማይገኝ ዕድል መሆኑን ተገነዘቡ። መሳሪያቸውን አነሱ፣ አፀዱ፣ አነገቡ፣ ስልጠናን ጀመሩ። ተጠቂ ሳይሆኑ አጥቂ መሆናቸውን ለራሳቸው ሰበኩ። ያስፈልጋሉዋ! መፍትሄ ናቸዋ! ተስፋ ናቸዋ!  

በዚህ ወቅት እርሶ የነበሩ ቢሆን፣ ከየትኛው ወገን ራስዎን ያገኙት ነበር? 

 

white-200.png

Serving Ethiopian women by encouraging and exemplifying vulnerable, thought-provoking conversations around the Gospel of Jesus Christ, the mission of the
Church, and the life of a Christian.

Address
:
Golagul Tower
Addis Ababa, Ethiopia

Emailinfo@selahethiopia.org
selahforethiopia@gmail.com

Follow Us

Subscribe to emails from Selah

We have officially launched our website and all our social media platforms. Please join us, follow, and share. Subscribe to our newsletter bringing you regular updates, resources, and everything in between!

Copyright © 2023 Selah Ministries.
Address: Addis Ababa, Ethiopia 
Emailinfo@selahethiopia.org